Page 1 / 1
ተሃድሶ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ
06/14/2011 4:39 am

Administrator
NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 1
Posts: 4
OFFLINE
በዚህ ፎረም ከዚህ የሚከተሉት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል
1)     ተሃድሶ አለ?
2)     ቤተ-ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል?
3)     የተሃድሶ  አላማ ምንድን ነው?
4)     እቅዱን እንዴት ያስፈፅማል?
5)     እስከአሁን በቤተክርስቲያን ላይ ያደረገው ነገር አለ?
6)     እስከምን ድረስ ይጓዛል?
7)     ተሃድሶን በበላይ የሚመራው ማን ነው?
8)     ተሃድሶ በምን ልንለያቸው እንችላለን?
9)     ትምህርታቸው ምንድን ነው?
10)     ክምእመናን ምን ይጠበቃል?
11)     ከበጋሻው ደሳለኝ ጋር ምን አለው?  
12)     ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ምን አለው?
................
ተሃድሶ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ

በዚህ ፎረም ከዚህ የሚከተሉት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል
1) ተሃድሶ አለ?
2) ቤተ-ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል?
3) የተሃድሶ አላማ ምንድን ነው?
4
Quote   
06/14/2011 4:41 am

Administrator
NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 1
Posts: 4
OFFLINE
(Biruk Teklu)በእግዚአብሄር ሰላምታ ሰላምታዬ ይድረስህ ብያለሁ ታምራት ስሜ ብሩክ ይባላል። በመጀመሪያ ይህን መልእክት እንድልክ የገፋፋኝ 1 በጋሻው ሊንክ ላይ የጻፍከው ሲሆን 2 ደግሞ በእድሜም ወጣቶች ስለሆንን በቤተክርስቲያን ጉዳይ ለመወያየት ያመቻል ብዬ ስላሰብኩ ነው/ፍቃደኛ ከሆንክ /።
ቤተ ክርስቲያን አሁን ያለችበትን ችግር ታውቃለህ። በተለይ በተሀድሶ እንቅስቃሴ ። እኔ ተሃድሶ የለም ከሚሉት ጋር ባልስማማም ነገር ግን ተሀድሶ ተብለው ከሚጠቀሱ ውስጥ ተሃድሶ ናቸው እንድል ምንም ምክንያት ያላገኘሁባቸው አሉ ። ምክንያት ሳታገኝ ደግሞ ሰዎችን ማውገዝ በህሊናም ሆነ በእግዚአብሄር ያስጠይቃል ። ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ችግር አላገኘሁባቸውም አላልኩም ችግሩ ግን የስነ ምግባር ችግር እንጂ የዶግማ ነው የሚል አስተሳሰብ የለኝም ። ለምሳሌ በጋሻውን እንውሰድ , በጋሻው አንተ እንዳልከው ብዙዎቻችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ምክንያት ነው። እኔ ወደ በቤተ ክርስቲያን በንስሃ መመላለስ ከጀመርኵ 5 ዐመት ይሆነኛል። የበጋሻውን ስብከቶቹን ከበፊት ጀምሮ እሰማ ነበረ እናም ስብከቶቹን ስሰማ በእግዚአብሄር መተማመንን፤ ተስፋ ማድረግን ፤ ንሰሃን እማር ነበርና በጣም ደስ ከሚሉኝ ሰባኪዎች አንዱ ነበረ / ሁሉም ስብከቶቹ አሉኝ/ ። ጎን ለጎን ደግሞ በጣም አወዛጋቢነቱን ደግሞ እመለከት ነበር
አወዛጋቢነቱ ግን ተሃድሶ እስከመባል ድረስ ያደርሰዋል ብዬ አስቤ እላውቅም። ተሃድሶ ከተባለ በኋላ ምን እንደምወስን ግራ ተጋብቻለሁ። ለቤተክርስቲያን እንዴት ብዬ ልቁምላት? በጋሻው ተሃደሶ ነውና ሊወገዝ ይገባዋል ልበል? እንዴት ብዬ; ምክንያቱም የበጋሻው የወንድሙነት ሰሜቴ ሊጠፋ አልቻለም በሌላ በኩል ደግሞ ተሃድሶን ያልሆነን ሰው ለማውገዝ መሞከር ሌላ ለ ቤተክርስቲያን ችግር መጨመር ነው። በተጨማሪ ችግርን ለመፍታት የምንሞክረው እንደ እግዚአብሄር ሃሳብና ፍቃድ እንጂ እንደ ቅንነታችን ነው ብዬ አላስብም። እኔ በበጋሻው ላይ የተነሳውን ተሃድሶ ለመባል ምክንያት ናቸው የተባሉትን መረጃዎች ማለትም ቅርብ ቀን የተለቀቀውን ሲዲ ጨምሮ ሁሉንም ለማየት ሞክሪያለሁ። እውነት ለመናገር ይህ ልጅ ትልቅ የስነምግባር ህጸጽ እንዳለበት ብመለከትም ተሀድሶ እስከ ማለት ድምዳሜ አላደረሰኝም።
እኔ ይህ ልጅ ቢመከር ለቤተ ክርስቲያን ከቆሙ እንደ ማህበረ ቅዱሳን ጋር ተስማምቶ እስከመስራት ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማል እላለሁ ስለዚህ መደረግ አለበት ብዬ የማስበው እንዴት ወደ አንድነት ማምጣት ይቻላል የሚለው ላይ ነው ። ቢሆንም እኔ የተሰማኝን ወደጎን እናድርገውና አንተ የተሰማህን እንወያይበት። ታምራት አንተ የገባህን ልጠይቅህ ; በጋሻውን የዶግማ ችግር አለበት ብለህ ካመንክ የቱ ጋር ስህተት እንዳደረገ ወይም እንደሻረ ብትንግረኝ /ማለቴ በየትኛው ስብከቱ / ? ሌላው ይህ ልጅ እንደነ ጽጌ ስጦታው አይነት ሰዎች ጋር በ አንድ ቤንች ላይ ሊቀመጥ /ሊፈረጅ / ይገባዋል ብለህ ታስባለህ ? የምትችል ከሆነ መልሱን አታዘገይው በተረፈ እኔ ይህን ምልእክት ወዳንተ የላኩት ሃሳቤን ለማጥራት እንጂ ለመከራከረ አይደለም። በቀረውስ በጣም በርታ ለኔም ጸልይልኝ ። ሁላችንም ሳንጎድል ለቤተክርስቲያናችን ለመቆም ያብቃን። ወስብሃት ለእግዚአብሄር።
................
ተሃድሶ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ

በዚህ ፎረም ከዚህ የሚከተሉት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል
1) ተሃድሶ አለ?
2) ቤተ-ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል?
3) የተሃድሶ አላማ ምንድን ነው?
4
Quote   
06/14/2011 6:05 am

NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 0
Posts: 1
OFFLINE
@biruk: Have you heard begashaw preaching these days?U know he said dont say Jesus is God...so u want him to be still continue preaching this non-sense???
Quote   
06/14/2011 2:44 pm

NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 0
Posts: 2
OFFLINE
i donot know what to say but ortodox is a great religion so we have keep this please . actually what biruk teklu is not clear with me because it was happend before some days ago but the solution is also as he (biruk teklu) says it is better to talk about it and facing challenge by developing us with the knowledge okey i am totally hopeful geting better ideas that makes us nice . pleas every body participate on this  thanks alot
Quote   
06/14/2011 4:31 pm

NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 0
Posts: 2
OFFLINE
@ hanna @ tamerat  ………………………………………………………………………………………………
……………ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር ነው!!!!!…………………
.በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚብሄር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሄር ነበረ ዮሀ1፥1 ።  ቃልም ስጋ ሆነ ዮሀ1፥12  ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር እንደሆነ ግልጽ አድርጎ ያስቀመጠ ነው ።  በጋሻው ይህን ያጣዋል ብዬ ማሰብ ይከብደኛል ።  ከዛም አንጻር በጋሻው ያለውን “ኢየሱስን እግዚአብሄር ወይም ስላሴ   አትበሉ”  ያለበት የዛን ሰአት /ቅጽበት/ ንግግር እኔ እንደገባኝ ኢየሱስ እግዚአብሄር አይደለም ለማለት ሳይሆን። የ ስም አገባቡን አስተካክሉ ለማለት ነው ብዬ ነው የወሰድኩት ። ይህን ጥቅስ እስቲ እንየው ፦ “ አንድ እግዚአብሄር አለና በእግዚአብሄርና በሰው መካከል ያለው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ” 1ጢሞ 2፥5። ብዙ ጊዜ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ይህንን ጥቅስ በመያዝ ኢየሱስ አማላጅ ነው ብለው ይናገራሉ ነገር ግን ይህ የተሳሳተ አተረጓጎም ነው ። ምክንያቱም ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ አንቀጽ ላይ መግለጽ የፈለገው አንድ እግዚብሄር አለና ማለቱ በስልጣን፤ በአገዛዝ ፤ በፈቃድ አንድ የሆነ  እግዚብሄር /የአለም ጌታ/ አለ ማለቱ ነው። በ እግዚብሄርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ  ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ማለቱ በአንድነት እግዚአብሄር ተብለው ከሚጠሩት ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ  ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው /ማእከላዊ/ የሆነ ማለቱ ነው። አለ ብሎ መካከለኛው አንድ ብቻ መሆኑን መግለጹ በተለየ አካሉ  ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በመሆኑ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሄር አብ መካከለኛ አይባልም  ለምን ቢባል ፍጹም አምላክ ብቻ ነው እንጂ ፍጹም ሰው አልሆነም ወደፊትም አይሆንምና እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስም መካከለኛ አይባልም  ለምን ቢባል ፍጹም አምላክ ብቻ ነው እንጂ ፍጹም ሰው አልሆነም ወደፊትም አይሆንምና ። ከዚህ አንጻር ነው እንግዲህ በጋሻው በተዋህዶ የከበረውን በእግዚአብሄርና በሰው መካከል ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በሉ  ለማለት ፈልጎ ይመስለኛል እንጂ አየሱስን አምላክ አይደለም ለማለት ፈልጎ ነው ብዬ አልወሰድኩትም ። አላዛርን ያስነሳው ወደ ቢታንያ የወረደው ማን ነው ስትባሉ እግዚአብሄር ከማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በሉ ያለበትም እይታ ከዚህ አንጻር ነው ብዬ የማስበው ። ይህ ማለት ግን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእብሄር አይደልም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ይመስለኛል ።                                        
ይህ እኔ የተረዳሁበት ምልከታ ነው። ልክ ነኝ ብዬም አልደመደምኩም ። ለመታረምም ለመማርም ሆኜም እግዚአብሄርም በቸርነቱ እንዲመለከተኝም እየጸለይኩ ይህን የተረዳሁትን ጽፌለሁ ።                                          
                                                                      
                            እግዚአብሄር በቸርነቱ ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን
                                     ወስብሃት ለእግዚአብሄር።
                                                            
Quote   
06/15/2011 7:27 am

Administrator
NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 1
Posts: 4
OFFLINE
@ብሩክ፦ ያነሳኅው ሃሳብ በጣም ጥሩ ነው ፤ ከመለያየት መስማማት መልካም ነው፡፡ ስለዚህ በጋሻውና የእርሱ ባልደረቦች ለቤተ-ክርስቲያን መልካም ከሚያደርጉ እንደ ማህበረ-ቅዱሳን አይነት አካላት ጋር ቢወያዩና ቢስማሙ መልካም ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ ለጥፋት ችክ ብሎ የተነሳ አካል ካለ እንስማማ ቢሉት ነገሮችን የበለጠ ለማበላሽት ከመሮጥ ይታቀባል ማለት ይከብዳል፡፡ ይህ ማለት ግን አሁንም በጋሻው ተሃድሶ ሆኖኧል ወይም የቤተ-ክርስቲያን ጠላት ነው ለማለት መድፈሩ የራስ ያልሆነን ስልጣን መተግበር ከመሆኑም በላይ በቂ ባልሆነ ምክንያት የራሳችንን ሰዋች ምናልባት እንድናጣ መጠንቀቅ ይገባል፤ስለሆነም በጋሻውና የእርሱ ባልደረቦች አሁንም ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ መልካም እረኞች ናቸው ብለን ብንነሳ መልካም ይመስለኛል፡፡ይህ ማለት ግን ቤተክርስቲያንን እናድሳለን እንለውጣለን አርጅታለች የሚሉ ከውስጥም ከእኛ ወገን ከውጭም ከፕሮቴስታንት አካባቢ የለም ማለት እጅግ ስንፍና ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ከበቂ በላይ መረጃወች አሉና፡፡ ለዚህ መሃበረ ቅዱሳን ያሳተመውን የተሃድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ላይ የሚለውን ወቅታዊ መፅሃፍ ማንበብ በቂ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ከሆነ ታዲያ በኛ ውስጥ ያሉት የተሃድሶ ቅጥረኞች እነማን ናቸው ማለትና ማጣራት የግድ ይሆናል፡፡ እነዚህን ለመለየት ደግሞ ያለው አማራጭ ትምህርታቸውንም ሆነ ተያያዥ ስራቸውን በጥንቃቄ ማየት ካልቻልን ተዋህዶን ከአደጋ መጠበቅ አንችልም ማለት ነው፡፡ በዚህ አግባብ በጋሻውንም ሆነ ዳንኤል ክብረትን ማየት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ እንደኔ እምነት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ትክክለኞቹ  የቤተ-ክርስቲያን መምህራንና ዘማሪያን በጥቂቱ ከዚህ የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
1)     ምንም አይነት የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ያልሆነ አዲስ አስተምሮ ማስተማር አይገባቸውም፡፡
2)     የቤተ-ክርስቲያን አባቶችን ትእዛዝ መጠበቅና ማስጠበቅ ይኖርባቸዋል(በተለይ የሲኖዶስን ውሳኔ)
3)     ትምህርታቸው ኦርቶዶክሳዊ መአዛ ሊኖረው ይገባል፡፡
4)     በየትኛውም አጋጣሚ የቤተ-ክርስቲያኗን ዶግማና ቀኖና የሚቃወም ተግባር መስራት አይገባቸውም፡፡ ወዘተ
እንግዲህ በዚህ በ4ቱ ብቻ በጋሻውን ብንዳኘው
1)     ቅዱስ ሲኖዶስ በጋሻውንም ሆነ ሌሎች በቤተ-ክርስቲያን  ተመዝግበው የማይታወቁ መምህራንን በየትኛውም አውደምህረት ላይ እንዳያስተምሩና እንዳይዘምሩ በተደጋጋሚ ከልክሏል፡፡ ይህን የሲኖዶስ ትእዛዝ በማን አለብኝነት ከሚሰሩ ሰወች ጋር በመተባበርና በመጣስ አሁንም ማስተማሩን አላቆመም፡፡ለምን?
2)     ዲቁናው በቅዱስ ፓትሪያርኩ ተሽሯል፡፡ ለምን?
3)     የቤተ-ክርስቲያኗን ቀኖና የሚያፈርስ ተግባር የሆነውን የፓትሪያርክ ሃውልት ላይ እጁ አለበት፡፡ ለምን?
4)     የኦርቶዶክስ  ቤተ ክርስቲያን አስተምሮ ከሌሎች (ከፕሮቴስታንት)  የሚለየው ስለቅዱሳን ፣ ስለፃድቃን ፣ ስለመላእክት ፣ ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለምእመናን ዘወትር ማስተማር በመቻሏ ነው፡፡ በጋሻው ግን እንዲህ ሲያደርግ በብዛት አይታይም፡፡ ለምን? እነዚህስ ከላይ ከተዘረዘሩት ሃሳቦች በጋሻውን ኦርቶዶክስ ነው ወይስ ፕሮቴስታንት የሚያስመስሉት፡፡
5)     አዲስ አስተምሮ፦ በዚህ ጉዳይ ላይ በበጋሻው ያየሁት ፀባይ ተዋህዶ ኢየሱስን አትሰብክም ብሎ ማሰቡ ይመስለኛል፡፡ ይህንንም በፃፋቸው ሁለት መፅሃፍቶቹም ሆነ ስብከቶቹ ዘወትር ለመግለፅ ይሞክራል፡፡ መልካም እርሱ ባየበት አተያይም ቢሆንና ልክ ቢሆን ስለ ኢየሱስ ሲያስተምር ማንን መምሰል አለበት? ተዋህዶን ወይስ ፕሮቴስታንትን? ተዋህዶ ኢየሱስ(መድሃኒት)  ከማለት ኢየሱስ ክርስቶስ (መሲሁ መድሃኒት) ማለትን ታበረታታለች (ይህ ማለት ግን ኢየሱስ ስህተት ነው ማለት አይደለም ከነ ሙሉ ክብሩ ስትጠራው እንጂ) ፤ የኔ ጌታ ከማለት የጌቶች ጌታ ትለዋለች ፣ አዳኜ ከምትለው መድሃኒአለም ትለዋለች፡፡ ወዘተ በዚህ አግባብ በጋሻውን እንዴት ታየዋለህ? የሆነ ሆኖ እነዚህም ነገሮች በጋሻውን የሚያስወግዙ ወይም የሚያስለዩ ናቸው ማለት አልችልም ነገር ግን የሚያስመክሩ ናቸው እላለሁ፡፡

ስለ ቪሲዲው ደግሞ አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው ብሎ ሲጠይቅ ምእመናኑ ብዙወቹ እግዚአብሄር አሉ ፡፡ ይህን ጊዜ ተናደደና እግዚአብሄር አትበሉ ፤ ስላሴ አተበሉ የሚለውን አስተማረ፡፡ከዚያም ለሌሎች አስተማሪወች እናንተም ስታስተምሩ አትፍሩ አለ፡፡ በመጀመሪያ ልክ ነው ወይ? ወይንስ አትፍሩ ማለት ምን ማለት ነው? ማንን ደስ ለማሰኘት ነው? ምእመናኑን ኦርቶዶክስ ለካ እስከዛሬ ተሳስታለች ማለት ነው እያለ እንዲያስብ ነው? የሆነ ሆኖ ትልቅ ስህተት ሰርቷል ብየ አስባለሁ፡፡ ይህ ስህተቱም ከአለማወቅ ይሆናል ፤ ወይንም ለማሳሳት ይሆናል፤ ለዚህ ደግሞ የተዋህዶ ልጅ ከሆነ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል፡፡ ለምን ስህተት ሆነ?  
አልዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው? ወይንስ እግዚአብሄር የሚለው ስም ከሶስቱ አካላት የማን ነው?ይህ ስም የአብ ብቻ ነውን? አባቶች እንዳስተማሩን ይህስ የሶስቱም የአንድነት ስማቸው ነው፡፡ እኛም እግዚአብሄር ስንል ፦ እግዚአብሄር አብ ፣ እግዚአብሄር ወልድ ፣ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ማለታችን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በጋሻው አልዛርን ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ ነው እግዚአብሄር አይደለም ሲል ምን ማለቱ ነው? ምስጢረ ስጋዌ የሚያስተምረን ምንድን ነው? ቃል ስጋ ሆነ ሲባል የቃል(የመለኮት) ገንዘብ ለስጋ ሆነ የስጋ(የትስብእት) ገንዘብ የቃል ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው፡፡ የስጋ ገንዘብ የነበረው መራብ ፣ መጠማት ፣ መድከም ፣  መተኛት ፣ መቁሰል ወዘተ እግዚአብሄር ወልድ በለበሰው ስጋ እነዚህን ገንዘብ አደረገ ማለት ነው ምክንያቱም ይህ የመለኮት ገንዘብ አልነበረምና መለኮት አይራብም ፣ መለኮት አይጠማም ወዘተ፡፡ የመለኮት ገንዘብስ ምንድን ነው? ሙት በስልጣን ማስነሳት ፣ በባህር ላይ መረማመድ ፣ በሁሉ ቦታ መገኘት ፣ ወዘተ ፡፡ በዚህ አግባብ እግዚአብሄር ወልድ ሞተ ስንል  በስጋ ሞተ እንላለን እንጂ በመለኮት ሞተ ደግሞ አንልም፡፡ መለኮት አይሞትምና፡፡ እንዲህ ካልን ግን የስላሴ መለኮት አንድ ነውና አብም ፣ መንፈስ ቅዱስም ሞቱ ደግሞ እንላለን? ነገር ግን ሞቱ በስጋ ስለሆነ ይህን ለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰጣለን፡፡ ነገር ግን የመለኮት ገንዘብ የሆነውን ሙትን በስልጣን ማስነሳት ኢየሱስ ብቻ ካልን ፦ መለኮት ደግሞ ከአንድ በላይ ነው በማለት አዲስ አስተምሮ ይሆንብናል፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት ያስነስው በመለኮቱ ስልጣን ስለሆነ ፤ ነገር ግን ስላሴ በመለኮት አንድ እንደሆኑ ይህ ትምህርታችን ነው ፤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ ስንልም ይህ አሃዱ ያልነው መለኮትን ነውና፡፡ ስለዚህ ስላሴ ግን በባህርይው አንድ መለኮት እንደሆነ  እናውቃለን፡፡አለበለዚያ ደግሞ በጋሻው የኢየሱስ ክርስቶስን ባህሪ ከፍሎ ከሆነ እንጠይቀው ፦ ኢየሱስ ክርስቶስ አልዛርን ከሞት ያስነሳው በቃል ገንዘብ ነውን? ወይንስ በትስብእት ገንዘብ? ነገር ግን እግዚአብሄር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ አንድ እንደሆነ እኛ የኦርቶዶክስ  ክርስቲያኖች እናምናለን፣ ቃልም ከስጋ ጋር በፍጹም ተዋህዶ አንድ ሆኗልና ሁለት ባህርይ ከሚሉት እንለይ፡፡ እንግዲህ የቃል ገንዘብ ለትስብእት እንደሆነ በመለኮቱ ሰማይና ምድርን የመላ ፣ በስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ እርሱ በመለኮቱ ስልጣን አልአዛርን ከሞት አስነሳው እንላለን ፤ የስላሴ መለኮትም አንድ ነውና ስላሴ ደግሞ አልአዛርን ከሞት አስነሳው እንላለን ፣ ይህም መለኮት የእግዚአብሄር አብ ነውና እግዚአብሄር አብ አልአዛርን ከሞት አስነሳው ደግሞ እንላለን፤ ለመንፈስ ቅዱስም ይህ ይነገር ዘንድ ይሆናል፡፡ መለኮት ከ ትስብእት ለአይን ጥቅሻ እንኳን እንዳልተለየው ፦ አንድ በሆነው መለኮት አብም መንፈስ ቅዱስም ወልድን በስራው ሁሉ አልተለዩትም ፤ እግዚአብሄር ወልድም ምንም ስጋን በመልበሱ በምድር ቢሆን በመለኮቱ ግን ከዙፋኑ አልተለየም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ አስነሳው ማለት ፍፁም ስህተትና የተዛባ አስተምሮ ነውና በጋሻው ተሳስቷል፡፡ይህ ማለት ግን እግዚአብሄር አብ ሞተ አንልም ፤ ወይንም እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ተሰቀለ አንልም፡፡ ምክንያት መለኮት አይሞትም ፣ አይሰቀልም፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄር አብ ፣ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ፣ ወይንም ስላሴ ሞቱ አንልም፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ወልድ በተዋሃደው ስጋ ስለእኛ ሞተ ፣ ይህንም የስጋ ድካም ለኛ ሲል ገንዘብ አደረገ ብለን እናምናለን ፡፡
ስለዚህ በጋሻው በብዙ ምክንያቶች የሚታየው መልኩ ከኦርቶዶክስነቱ ይልቅ ተሃድሶነቱ ስለጎላ ፣ ይህም ብዙወቹን ሊያሳስት ስለሚችል ፤ ስህተቱን አውቆ መማር እንዲችል ፣  በቤተ-ክርስቲያንም የማገልገል ፈቃድ ተቀብሎ እኛኑ መስሎ ቢያስተምር መልካም ይመስለኛል፡፡  ለማንኛውም ይህ ፎረም የተዘጋጀው ቤተ-ክርስቲያናቸውን የሚወዱ ወጣቶች ተዋህዶን ከተኩላ ለማዳን ሆኖ በጎችን ግን ተሳስተን ተኩላ ናቸው እንዳንል ፦ በአንድ ሰው ላይ ክስ ወይም ተቃውሞ ሲቀርብ ከመፍረድ ይልቅ ማስረጃው ምንድን ነው ማለቱ አዋቂነት ይመስለኛል ለዚህም ብሩክ ልትመሰገን ይገባል፡፡
................
ተሃድሶ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ

በዚህ ፎረም ከዚህ የሚከተሉት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል
1) ተሃድሶ አለ?
2) ቤተ-ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል?
3) የተሃድሶ አላማ ምንድን ነው?
4
Quote   
06/16/2011 3:24 pm

NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 0
Posts: 2
OFFLINE
okey my freinds i think i have to strat  by saying all guys thanks alot for ur participation. when i enter to my idea is yes offcorse what begashaw says is hard to belive if he says correctly like that .what i mean is when i am talking with another persons they totaly donot belive what he saied they said to me that is the film editing not the reality show or he didnot preaching like that so  TAME OR another person who is in this forem please i want to proof this thing because to be sure and conclued on  begashaw is not ours that means he is an tehadiso. at last who are the followers of him if he is tehadiso y i ask u guys this is last day i heard the news of the weeding of fikadu there was a fighting againist them  y they do that means is that the last option to kick them i do not think so anyways wendimoche na ehitochie  tell me more about that . thanks for all
Quote   
06/17/2011 4:43 pm

NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 0
Posts: 2
OFFLINE
@ tamerat ወንድሜ ታምራት አስተያየትህን አንብቤዋለሁ ሃሳብህንም ለመረዳት ሞክሪያለሁ ቢሆንም በጋሻውን የመዘንክበት ክፍል  ለእኔ ትንሽ ተወሳስቦብኛል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ምንም የተጣራ ነገር ለማየት በመቸገሬ ነው፡፡ አንተ እልዳልከው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በጋሻውን እንዳያስተምር እየከለከለው አሁን ማስተማሩ፤ ድቁናው በፓትሪያርኩ ተሽሯል ተብሎ እሱ ግን መጋቢ ሐዲስ መባሉ፤ እንዲሁም ተሻረ የተባለው ዲያቆን ደግሞ በፓትሪያርኩ የሐውልት ሥራ ላይ ቦታ ማግኘቱ እንዲሁም በሐውልት ምርቃት ላይ በአውደ ምህረት ላይ ፓትሪያርኩ በተገኙበት (ድቁናውን መሻራቸውን ሳንረሳ) መገኘቱና የመሳሰሉትን ለማየት የነገሩን ችግር ጥልቀት  ከታች ሰባኪ ወንጌል እስከ ፓትሪያርኩ ድረስ የሚመለከት ጉዳይ ስለሆነ በዚህ ነገር ላይ ብዙ ሃሣብ ባልሰጥበት ደስ ይለኛል፡፡
     ሌላው ያነሳኸው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከፕሮቴስታንት የሚለየው ስለ ቅዱሳት፣ ስለ ፃድቃን ለምዕመናን ማስተማሯ ነው፡፡ ለእኔ ግን ኦርቶዶክስ፣ ስለ ቅዱሳን፣ ስለጻድቃን ባታስተምርም እንኳን ከፕሮቴስታንት ጋር በሌላ በምንም ትመሳሰለች ብዬ አላስብም፡፡ እኛም ስለመላዕክት ስለጻድቃን ስናስተምር ከፕሮቴስታንት ለመለየት ብለን ሳይሆን ማስተማራችን እግዚአብሔር ስለሚከብርበት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡
     ስለዚህ በጋሻው እነዚህን አለመስበኩ ፕሮቴስታንቶችን ያስመስለዋል ብለን ከመደምደማችን በፊት ፕሮቴስታንቶችን ባይኖሩ ኖሮ ምን ያስብለዋል ብለን ብንወስደው ለእኔ እንደሚመስለኝ ቸልተኝነት እንዲሁም አለማስተዋልና መዘናጋት ነው ብዬ እወስደዋለሁ፡፡ አሁን አሁን በአንድ አንድ ሰባኪያን ዘንድ እየታየው ያለው ነገር ምንድን ነው መሰለህ በክርስትና ሕይወትን በማነጽ ላይ ያተኮረ ሆኗል፡፡ ቢሆንም ግን ሁሌም ስለሕይወት መስበክ እና ሌሎችን መተው ከስህተት አያልፍም፡፡
     ተዋህዶ ኢየሱስ ክርስቶስን የእኔ ጌታ ከማለት የጌቶች ጌታ ትለዋለች፡፡ አዳኜ ከምትለው መድሐኒዓለም ትለዋለች ብለሃል፡፡ የጌቶች ጌታ ስትለው ግን የእኔ ጌታ አትበሉ አላለችም፡፡ መድሐኒዓለም ስትለው አዳኜ አትበሉት እንዲሁ አላለችም፡፡ ነገር ግን ጥያቄ ውስጥ ሊገባ የሚገባው ሰዎች በተለየ መልኩ መድሐኒዓለም (የዓለም መድሐኒት) አይባልም ቢሉ ግን ስህተት ከመሆን አያልፍም፡፡
ስለ ቪሲዲው ደግሞ አሁንም ቢሆን በጋሻው ለማለት የፈለገው በግልጽ የተገነዘብከው አልመሰለኝም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በጋሻው ኢየሱስ እግዚአብሔር ወይም ሥላሴ አይደለም ለማለት አይደለም የፈለገው (ይህ እኮ ትልቅ መሠረታዊ የዶግማ ስህተት መሆኑን አንርሳ) ይህንንም ትልቅ የዶግማ ስህተት ሰዎች በተሰበሰቡበት ለመግለጽ የሚደፍር ተሐድሶ አለ ብዬ አላስብም ካለም ዳግም ወደ ዐውደ ምህረቱ ልመለስ ይላል ማለት ትንሽ ይከብዳል ፡፡ ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ እስቲ አንተን ልጠይቅህ ለሙሴ የተገለጠለት ማን ነው ብልህ እግዚአብሔር ትለኛለህ ወይስ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለአብርሃም በቤቱ የተገኘው ሥላሴ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብልህ አንተ ማን ትለኛለህ? ምንም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ቢሆንም እንደ ስሙ አገባብ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማይባል እርግጥ ነው፡፡ እኔ እንደገባኝ እግዚአብሔር ሰው የሆነበት የተዋህዶ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም መሆኑ ነው፡፡ መጽሐፍ እንዲህ እንደሚል “ አንድ እግዚአብሄር አለና በእግዚአብሄርና በሰው መካከል ያለው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ” 1ጢሞ 2፥5 /እባክህ ይህን ጥቅስ በሚቀጥለው ጊዜ አሁን ካነሳነው እርስ ጋር አያይዘህ ለማብራራት ሞክር/፡፡ ስለዚህ አላዛርን ማን ነው ከሙታን ያስነሳው ቢባል ምንም እንኳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆንም እግዚብሔር ከማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ማለቱ ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ እንደተረዳሁት አራቱም ወንጌላዊያን በተዋሐዶ የተከበረውን አምላክ (እግዚአብሔር) አንድም ቦታ እግዚአብሔር የሚለውን ስም ሲጠቀሙ አላስተዋልኩም፡፡ ከዚያ ይልቅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም በሁሉም ቦታ ተገልጾአል፡፡ የእግዚአብሔር ስሙ ስንል በብሉይ ለሙሴ፣ ለኤልያስ፣ ለአብርሃም የተገለጠውን ያስታውሰናል፡፡ ኢየሱስ ክርክስቶስ ስንል ደግሞ በድንግል ክንድ የታቀፈውን ከሐዋርያት ጋራ የተመላለሰውን ኢየሱስ ክርስቶስ (እግዚአብሔርን) ያስታውሰናል /ይህ ማለት ግን አሁንም የስም አገባብ ላይ ነው ትኩረቴ/ ፡፡ ስለዚህ እዚህ ጋር ለመግለጽ የተሞከረው በብሉይ የምናውቀውን እግዚአብሔር እና በአዲስ ኪዳን የተገለፀውን እግዚአብሔር በደንብ በአስተውሎት ለመረዳት እንጂ አንተ እንደመሰለህ (እንደተገነዘብከው) ባህሪውን ለመከፋፈል አይደለም ወይም ሁለት ባህሪ ለማድረግ አይደለም፡፡   በተረፈ እኔ ለበጋሻው ጥብቅና የመቆም ፍላጎት ኖሮኝ ሳይሆን በተለይ አሁን በብዙ ሰዎች ዘንድ ይታያል ያልኩትን የተዛባ አመለካከት ለቤተ ክርስቲያን ችግር ያመጣል ብዬ ስላሰብኩ ነው ፡፡
  
Quote   
06/18/2011 11:26 am

NEWBIE


Regist.: 06/18/2011
Topics: 0
Posts: 1
OFFLINE
@ biruk. don't you witness the name "EGZIABHER" being used by WENGELAWUYAN to mean "EYESUS KIRISTOS"?
READ AT ACT.20:28 "EGZIABHER BEDEMU YEWAJATN BETEKIRSTIAN.....
JOHN. 9   "YIH SEW EWUR HONO YETEWELEDEW YE'EGZIABHER SIRA BE'ERSU ENDIGELETS ENJI....
BIZU ALU... BETINIKAKE YINEBEBEU
Quote   
06/19/2011 3:22 am

Administrator
NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 1
Posts: 4
OFFLINE
ሰላም ብሩክ፦ ፖስት ያደረከውን መልእክት ተመለከትኩት ፣ ነገር ግን ከመወያየት ይልቅ መከራከር እንዳይሆን እፈራለሁ ፤ ለዚህ ነበር የመጀመሪያ መልእክቴን በውይይት መንፈስ የፃፍኩት፡፡ የሆነ ሆኖ ክርክር የሚያደርጉ ሰወች ተከራካሪው ለማለት የፈለገውን ሃሳብ ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ክርክሩን ለማሽነፍ ጉድለትና ስህተት ለማገኘት ይጥራሉ፡፡ ስለዚህም በመልካም ተግባሮች ላይ የተሻለ ስራ ለመስራትም ሆነ አዲስ አስተሳሰብ ለማስረፅ ከመከራከር ይልቅ መወያየቱ በተለይም ለቤተክርስቲያናችን የወቅቱ ሁኔታ በጣም ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉንም ነገር ዝም ብሎ መቀበል ጥሩ ነው ማለት አይደለም ፤ ነገር ግን የሰወችን ሃሳብ በበጎ አይን እያዩ የጎበጠውን እያቃኑ ፣ የተጣመመውን እያስተካከሉ መነጋገሩ መልካም ነው፡፡
በተረፈ ስለበጋሻው ስናገር መልኩና ሁናቴው ኦርቶዶክስ ከመምሰል ፕሮቴስታንት መሰለብኝ ያልኩባቸውን ሃሳቦች አንተ እንድትረዳልኝ ብቻ የጠቀስኳችው ከብዙው ጥቂቱን ነበር ፤ እነዚህን ስጠቅስ ደግሞ ተሳስቼም ቢሆን ስለ ግል ህይወቱ አላወራሁም፡፡ ደግሜ ደጋግሜ እንደተናገርኩትም በጋሻውን ተሃድሶ ወይም ፕሮቴስታንት ነው አልልም ብያለሁ፣ ምክንያቱም ይህ የኔ ስልጣን አይደለምና ፤ ነገር ግን በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ተነስተው የነበሩ የመናፍቃን እንቅስቃሴወችን ሲታገሉና ሲረቱ እንደነበሩት ቅዱሳን አባቶቻችን ፦አርበኛ ሁነው ከሚመሩ የዘመናችን ታማኝ የቤተክርስቲያን ጠበቃወች (ለምሳሌ ማህበረ ቅዱሳን) ጋር በመሆን  ቤተክርስቲያንንና ቤተክርስቲያንን ብቻ በማስቀደም የምንችለውን ሁሉ በክርስቲያናዊ ስነምግባር ለማድረግ መሰለፋችን አላማው በጎ ነውና ከእግዚአብሄር በረከትን እንጂ መርገምን እንደማናገኝ በእርግጠኛነት መናገር እንችላለን፡፡ 318ቱ ቅዱሳን አርዮስን አውግዘው ሃይማኖትን ሲያፀኑ ክርስቶስ ሊባርካችው ከመሃላቸው ተገኘ እንጂ አልቀሰፋቸውም፡፡ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ በዘመኑ ተነስተው የነበሩ መናፍቃንን ሲቃወምና ተዋህዶን ሲያፀና ቅዱስ ተባለ እንጂ ርጉም አልተባለም፡፡ ነገር ግን እነዚያ ሊቃውንት በአርዮስና በተከታዮቹ ሲወገዙ ምናልባትም ክርስቲያናዊ ፍቅር የሌላቸው ከንቱወች ተብለው ይሆናል፡፡ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅንም ለተዋህዶ ጠበቃነት በመቆሙ መናፍቃኑ ሲሞት መግቢያው ሲኦል ነው ብለውት ይሆናል፡፡እኒህ የኛ አባቶች ግን ክርስቶስ ከቤተመቅደስ  እቃ ሻጮችን ባስወጣበት መንፈስ ለቤተክርስቲያን በመቅናት ህይወታቸውን በመስጠት ታገሉ፡፡ ይህ መንፈስ ያልገባቸው ሰወች ግን እነዚህን አባቶች አንዲትን ዝሙተኛ ሴት ሊወግሩ ከተሰበሰቡ የአይሁድ ማህበር ጋር ይደምሯቸዋል፡፡እኒህ ፃፎችና ፈሪሳዊያን እነርሱ በሃጢያት ተተብትበው ራሳቸውን ግን በሙሴ ንፅህና ትክክል የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እኒህ የኛ ቅዱሳን ግን ህይወታቸው ክርስቶስን መስሎ ራሳቸውን ግን ሃጢያተኛ አድርገው ነውና ይለያያሉ፡፡ እነዚያ ከቤተመቅደሱ የሚያገኙት ገንዘብ ስላነሳቸው ይጮሃሉ ፤ እኝህ የኛ ቅዱሳን ግን ለሰረቃቸው ይህን ደግሞ ረስተሃልና ወሰድ የሚሉ  ፣ ቀኛቸውን ሲመቷቸው ግራቸውን የሰጡ ፣  ስለራሳቸው ምቾት አንድም ጊዜ የማይጨነቁ፣ ፍቅርን ክርስቶስን በመምሰል የሚያውቁ ሲሆኑ ፦ ቤተክርስቲያናቸውን ከመናፍቃን እየጠበቁ ተኩላወችን ሲያባርሩ ግን እኒህ የክርስቲያን የፍቅር መንፈስ የሌለባቸው የሚላቸው ማን ነው? እንግዲህ ብሩክ ይህን ሁሉ የምልህ ራሴንና የሚመስሉኝን ላፀድቅ አይደለም ፤ ነገር ግን ስለሰወች የግል ህይወት መፈትፈት ያልሆነ ፤ ግን ስለ ቤተክርስቲያን መጠበቅ እድሜአቸውን ሙሉ የደከሙትን አብነት አድርገን ፣ ዲያቢሎስ ይህችን ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደሚዋጋት አውቀን ፣ በክርስቲያናዊ ስነምግባርና እውቀት ሆነን መታገል ፅድቅ እንጂ ግብዝነት አይደለም፡፡ይህንም ትምክህታችንን ማንም ከንቱ እንዲያደርግብን አንፈቅድም፡፡  ይህን ሁሉ እየሰሙም ዝም ማለት ከመንፈሳዊነት ዝለት የተነሳ የሚመጣ እንጂ ፅድቅም አይመስለኝም፡፡ ደግሜ ይህን የምለው ግን በቅንነት እንደአንተ ስለቤተክርስቲያን ክብር የቆሙትን ልተች አይደለም ፤ እነዚያን ሩቅ ሆነው ፍቅርንና ስለቤተክርስቲያን መቆርቆርን የማያውቁትን ነገር ግን ሳያውቁት ለጠላት የሚገዙትን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው እንጂ፡፡
ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ ፦ በክርክር መንፈስ ባልሆነ ወንድማዊ አስተያየት አንተ ያነሳሃቸውን ሃሳቦች እስኪ እንወያይበት፡፡ በጋሻው በፓትርያርኩ ዲቁናው ተቀምቷል ፡ እርሱም  በፓትርያርኩ ላይ ከፍተኛ ትችት በመፅሃፉ ላይ ፅፎ ሲያበቃ በምን ምክንያት ለፓትርያርኩ ሃውልት ስራ ከፍተኛ አስተዋፆኦ ሊያደርግ ቻለ? ለዚያውም የቤተክርስቲያኗን ቀኖና አፍርሶ፡ ለምን? እስኪ ይህን በደንብ አስብበት ምን ፈልጎ ሃውልት አሰራ? ይህ የሃውልት ስራ እኮ እጅግ ስህተት እንደሆነ በዚህም ቤተክርስቲያን አንገቷን እንደደፋች ከእኔና ካንተ በላይ ራሱ በጋሻው ያውቃል፡፡ ታዲያ ዲቁናውን እንዲመልሱለት ነው? ወይስ ሲኖዶሱ እንዳያስተምር ስለከለከሉት ፈቃድ ለማግኘት ይሆን? ወይንስ ለምንድን ነው? ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ በዘመኑ የነበረው ንጉስ ለራሱ ሃውልት አሰርቶ በአደባባይ ማስተከሉን ቢመለከት ይህ ክርስቲያናዊ አለመሆኑን በግልፅ ተናግሮ ሃውልቱን እንዲያነሳ ለንጉሱ ቢያሳስበው ንጉሱ ተቆጥቶ በጠላትነት እንደተነሳበት በጋሻው አልሰማ ይሆን? እኔስ ከበጋሻው የቅዱስ ዮሃንስ ግብር ይበልጥብኛል፡፡ግን ምንም ይሁን ሲኖዶስ እኮ ከልክሎታል፡፡ ታዲያ ከሲኖዶስ አስበልጠን እሱን መስማት ይገባል ትላለህ? ታዲያ በጋሻው አስቀድሞ ክልክልና ስህተት ነገሮችን ከመፈፀም ይልቅ ቅዱስ ሲኖዶስ እንዳዘዘው ትእዛዙን አክብሮ ራሱን ቢያፀዳ መልካም ሆኖ እያለ በትእቢት በሚመስል ራሱን ከፍ አድርጎ ከህግ በላይ ማድረግ መሞከር ክርስቲያናዊ ግብር ይመስልሃል?
ሌላው ደግሞ እንዴት እንዳየኅው ያልተረዳሁት ፦ አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ ነው ማለትና አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ ብቻ ነው እግዚአብሄር ወይም ስላሴ አትበሉ የሚለው ይህ አንድ ነውን? ወንድሜ፦ በጋሻው ይህን ሲል አውቆ ለማሳሳት ነው ለማለት አልደፈርኩም፡፡ እንዳልኩትም ተሳስቶ እንደሆነ ይቅርታም ጠይቆ ቢሆን ብያስተካክል መልካም ነው ነው ያልኩት፡፡ አንተ ግን እንደመሰለኝ ይህን ስህተት የለበትም አልክ? ያቀረብከውን ማብራሪያም ይህን ያስረዳል ብየ አላስብም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ አካላዊ ቃል ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ስለእኛም ቤዛ ሆኖ እንደተንገላታ መፃህፍት ያስረዱናል፡፡የስም አጠራሩ ክብር የሚገባው እርሱ ይህን ስም በተዋህዶ በፍፁም አንድነት ለከበረው ሰውነቱና አምላክነቱ የተሰጠ ከስሞች ሁሉ  በላይ የሆነ ስም ነው፡፡ ይህን ስም ስንጠራ በሰውነቱ የደከመውን በመለኮቱ ግን ሃያል የሆነውን እግዚአብሄር ወልድ እንጠራለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስንል ግን እግዚአብሄር አብ ወይንም እግዚአብሄር መንፈስቅዱስ ማለታችን አይደለምና ኢየሱስ ብቻ ስንል አብም ሆነ መንፈስ ቅዱስን አይጨምርም ማለታችን ነው፡፡ ይህች “ብቻ” የምትለው ቃል በኢየሱስ ላይ ሲቀጠል ይህ እርሱ በትስእብቱ ገንዘብ ያደረገውን ያጠይቀናል፡፡ ይህም የሞተው ኢየሱስ ብቻ ነው ብንል አብም ሆነ መንፈስ ቅዱስ አልሞቱም ማለት ስለሆነ ይህ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን በመልኮቱ ስልጣን ያደረገውን ተግባር ኢየሱስ ብቻ ማለት ስህተት ነው ምክንያቱም መለኮት አንድ ነው ይህንም መለኮት አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም የአንድነት ገንዘባቸው ነውና፡፡ስለዚህ አላዛርን ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ ብቻ ነው ማለት ስህተት እንደሆነ በራሳችን ፍልስፍና ባልሆነ በእነ ቅዱስ ቄርሎስ ትምህርት እንደዚህ ማስረዳት እንችላለን፡፡ምክንያቱም አላዛርን ከሞት ያስነሳው በመለኮቱ ስልጣን ስለሆነ፤ ስለ ኢየሱስ መካከለኛነት የተጠቀሰውም ስለ ሰውነቱ የስጋው መቆረስ የደሙ መፍሰስ ንፁህ መስዋእት ሆኖ የማስታረቅን ተግባር በሰውና በእግዚአብሄር መካከል የሆነ ተባለ፡፡ ይህም በእግዚአብሄር ተባለ እንጂ በእግዚአብሄር አብ ብቻ አልተባለም፤  እግዚአብሄርም ሲባል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን እንደሆነ የአለምን ሃጢአት በሙሉ በሰውነቱ ተሽክሞ ከራሱ ጋር ፣ ከአባቱ ጋርና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀን ብለው ኣባቶች አስተማሩን፡፡ይህን የማስታረቅ ተግባር በሰውነቱ መሽከሙ ደግሞ ግድ ነበር ይህም ለመለኮት ይነገር ዘንድ አይገባምና፡፡ ምክንያቱም መለኮት ይቅር የማለት እንጂ የማማለድ ና ዝቅ የማለት ባህሪ ገንዘቡ አይደለምና፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋሃደው ስጋው ስለኛ ተዋረደ፡፡ ዝቅም አለ ፤ እንደ አይሁድ ክህነት ያልሆነ  ሃጢአት የሌለበት ንፁህ በመሆኑ ስለራሱ መስዋእትን ማቅረብ ሳያስፈልገው ስለኣዳም ልጆች ግን ራሱን ዝቅ አድርጎ ነፍሱን ስለበጎቹ መስዋእት አድርጎ ሰጠ፡፡ ይህስ መሞቱ በስጋው ስለሆነ አብም መንፈስ ቅዱስም ሚና የላቸውም ማለት ግን አይደለም፡፡ ሰው ይድን ዘንድ አብ ስለወደደ መንፈስ ቅዱስም ስለፈቀደ ወልድም ደስ ስላለው አንድ በሚሆን የፈቃድ አገዛዛቸው መወለድ ግብሩ የሆነ ወልድ ሰውን አምላክ ሊያደርግ ወረደ እንጂ ማንም ወልድ ከአብ የበለጠ ሰውን ይወዳል አይበል፡፡ መንፈስ ቅዱስም ሰውን እንደወልድ አይወድም አይባል፡፡ ይህ የመለኮት ፈቃድ አንድ ነውና በዚህስ አንለያይ፡፡ ስለዚህ ነው ኢየሱስ “ብቻ” ማለት ስህተት የሚሆነው፡፡
ብሩክ ሌላው ሌላውን ላንሳው ይሆን? ወይንስ ከመፃህፍት ማስረጃ በቀጥታ ልጥቀስልህ? አላዛርን ያስነሳው በምድር የነበረው ኢየሱስ ብቻ ነው ካልከኝ ፦ ቅዱስ ጴጥሮስ “እግዚአብሄር በደሙ የዋጃትን ቤተ-ክርስቲያን “ ሲል ተሳስቷል ማለት ነው?ደሙ የፈሰሰው ኢየሱስ እንደሆነ እያወቅን! ስለዚህም በበጋሻው ትምህርት “እግዚአብሄር በደሙ የዋጃትን ቤተ-ክርስቲያን የሚለውን ኢየሱስ ብቻ በደሙ የዋጃትን ቤተ-ክርስቲያን” የሚለውን እናገኛለንና ቅዱስ ጴጥሮስ ተሳስቷል ማለት ነውን? ወይንስ ቅዱስ ዳዊት “እግዚአብሄር በመለከት ድምፅ አረገ” ሲል ይህ እንዴት ይሆናል? ወንጌላውያን እንደነገሩን ኢየሱስ እንዳረገ ስናውቅ፡፡ስለዚህ “እግዚአብሄር በመለከት ድምፅ አረገ የሚለውን በበጋሻው ትምህርት ኢየሱስ ብቻ በመለከት ድምፅ አረገ” ማለታችን እንደሆነ በዚህም ቅዱስ ዳዊትን ስህተተኛ ማድረጋችን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ፍፁም ሰው ብቻ ያይደለ ፍፁም አምላክም እንደሆነ የእግዚአብሄር ልጅ የማርያም ልጅ እግዚአብሄርም እንደሆነ በተረዳ ነገር አውቀነዋልና ኢየሱስ ብቻ ለማለት የሚደፍሩትን ምን እንላቸዋለን? ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ያደረገው ነገር ሁሉ በስላሴ ፈቃድ እንደተደረገ  ስናውቅ ኢየሱስ ብቻ ይህን አደረገ ለማለፅ ምን ያስፈልጋል? ከአብ አብልጠን ወልድን እንወደው ዘንድ መፃህፍት የት ቦታ አስተማሩን? ወይንስ ኢየሱስ ብቻ ስንል እኔ እና አብ አንድ ነው የሚለውን ወዴት ልንወስደው ነው? ይህን ሁሉ የምለው ግን በጋሻው ይህን ሲናገር ተሳስቶ ይሆናል የሚለውን ግንዛቤ ውስጥ በማድረግና እንዲህ ለሚያምኑት ግን ይህ የተዋህዶ እምነት እንዳልሆነ ለመግለጥ ነው፡፡
የሆነ ሆኖ እስኪ መልስልኝ በጋሻው በሲኖዶሱ ለምን ተከለከለ? ወይንስ ለምን ስርአት ይዞ አያስተምርም? በጋሻው ለምን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ይጣላል? ለምሳሌ (በአንድ ወቅት ደም አፍሳሽ ማህበር ሲል ጠቅሶታል፡፡ ለምን?)፡፡ ብዙወቹ ትምህርቶቹና የመዝሙር ግጥሞቹ ከፕሮቴስታንት መምህራንና ዘማርያን የተገኙ(የተቀዱ) ናቸው፡፡ (ለእነዚህ ማስረጃ ካስፈለገህ ማገኘቱ ከባድ አይመስለኝም የአደባባይ ምስጢር ነውና)ለምን? አንድ የናይጄርያ ፓስተር ስብከት እጅግ አዋጭ ቢዝነስ ነው እንዳለ በዚህ አግባብ በጋሻውን እንዴት ታየዋለህ? ታዲያ እኒህ ሁሉ ግድፈቶች እያሉና ተሃድሶወች ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እየጣሩ ባሉበት ሰአት በጋሻው ምንነቱን ለይቶ ይታወቅ ማለት ግዴታ አይመስልህም? ነገር ግን ይህን ሁሉ ስለአንድ ሰው ማውራታችን ወደአንድ ሃሳብ እንድንመጣ ከረዳን ነው እንጂ ተዋህዶስ ባንድ ሰው ምን ትሆናለች ብሎ አብዝቶ የሚጨነቅ ማን ይኖራል?
ወስብሃት ለእግዚአብሄር
................
ተሃድሶ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ

በዚህ ፎረም ከዚህ የሚከተሉት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል
1) ተሃድሶ አለ?
2) ቤተ-ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል?
3) የተሃድሶ አላማ ምንድን ነው?
4
Quote   
06/19/2011 7:28 am

NEWBIE


Regist.: 06/19/2011
Topics: 0
Posts: 1
OFFLINE
I read the discussion! It is very good to exchange views. I am not sure whether each topic will be seen separately. For the time being let me say what i feel. The discussion should not be focused on a single individual. Yes there are notable persons who can mislead the public. But the danger over our holy church is not only a task of one individual. It is a coordinated effort. I think it is not a simple attack on the church only. It is an attack even on the traditions of the country. One healthy, rational Ethiopian can not accept degrading Saint Yared`s Zema. One healthy Ethiopian cannot be against the `traditional` philosophy (Kine).All human being has an obligation to protect and preserve all indigenous knowledge, performances, ways and rituals.

Especially for all followers of Orthodox Tewahido, it is not only culture, tradition and dignity. It is all about saving soul to Heaven! We have passed to 2000 years and we have saints passed with in the same process. After all who are we to change all of our Heritages. We know that our fathers and fore fathers receive the faith with all its rituals and they have also transfer for us with out change. They have make great care not to modify what they have received. We should not change what we receive.

I think most of us will agree that our church is full of every thing and no need of creating new things. And i think we all agree on the presence of Movement of Reformation! What most of us losing is that the Reformists are not making their agenda in a way that all ordinary person can understand. If one is very attentive in day to day affairs of the church, he can easily know who is doing what! But if he is simply listen Audio, video, Magazines and books, I have a fear that he may not be able to get the real picture. Style of preaching, Content of the preaching, way of acting can be justified. Most things have a risk of being justified. One who claims to be a rational person but far from participating in the process may not be in a position to identify errors! Because they are made in a very calculative manner so that `ordinary` person may not understand its long term effects.

To make my point clear, let me cite one example, Preaching about , kibrena Misgana Yigbawuna ,our Lord and God Jesus Christ, in all times may not have problems. One can justify by supporting many bible verses and so on. But we are missing important elements. We have to be very critical. First we have to ask whether it is the way our fathers, `liqawunts`, way of teaching. If it is not we have to begin questioning. I am not stating some language problems occurred out of good faith or due to second language problems. That is not! It can be rectified and be corrected as far as there is good will. Or some times gospel may be delivered as per the traditions with out losing its substance. We are talking about intentional, strategic teachings who have its own desired effects. If our fathers incorporates stories from `Gedlat`, `Dirsanat`,` Tamirat`, they may have their own purpose for doing so! I need not to justify their concrete reason. Because they can have sufficient explanation. But We know one thing. We have got teachings about faith and religion from our fathers. They have spent 10,20,30,40 years in education and more than that they are very humble and live Christianity as it ought to be. They have lived for the sole purpose of the words of the Bible, with out having economic or political Agenda. The Puzzle is whether i accept new methods or the previous ones. I don’t have a choice. We, and our contemporary preachers who have new style and substance can not exceed our fathers. I prefer a preaching who incorporates the stories and miracles of saint George! The miracles made to `Afomia` ,the life and miracles made by  of our Holy Virgin Mother.

Because that is what our fathers has done for 2 thousand Years. Do we think that they are so foolish? No they are full of wisdom. Do we think that they have done it because they are ignorant about the Gospel? No I know fathers knowing it even in their mind and can quote verses easily like a computer! Do we think that they were not preaching under the guidance of the Holy sprit?`` No they not merely know the gospel, they also live in it. They do not speak like a worldly orator. But their mouth were golden who have said about our God and all of its work from the bottom of their heart. They were not just Stage Performers. They were not script tellers. They say what they believe and live. That is why I look only to them.

ለምን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽህና፤ድንግልና፡አማላጅነት ለማስተማር ወይም ለመስበክ ይተናነቃቸዋል፡፡አባቶቻችን ከ 6 እና 7 አምት በፊት በእንባ ስለ ድንግል ማርያም የሚያሰተምሩንን ትምህርት የትኛዉ አዉደ  ምህረት ሂደን ተምረን በቃል ኪዳኗ እንጽናና፡፡የነ አባ ጊወርጊስን፡የነ ቅዱስ ኤፍሬምን የነ አባ ሕርያቆስን ከጣእማቸዉ ብዛት አጥንትን የሚያለመልሙ ትምህርቶች የትኛዉ ጉባኤ ማግኜት ይቻላል፡፡ወንጌልን በተግባር የተረጎሙልንን የሰማእታትን ገድልና ትሩፋት፡ራሳቸዉን የካዱትን መስቀሉን የተሸከሙትን ምድራዊያን መላእክት የተባሉትን የነ እንጦንስ፡የመቃርስን ጽናትና ተጋድሎ የሚነገረን እንፈልጋለን፡፡ልክ እንደ አባቶቻችን!!!
Quote   
06/19/2011 10:18 am

NEWBIE


Regist.: 06/19/2011
Topics: 0
Posts: 1
OFFLINE
ሁለታችሁንም (ታምራትና ብሩክን) ማመስገን እወዳለሁ:: በተቻለ መጠን ግን ክርክር እንዳይሆን አንዱ የጻፈውን ሌላው በደንብ ሊረዳው ይገባል:: የብሩክን የመጀመርያውን ጽሁፍ አንብቤ አስተያየት/መልስ ለመጻፍ ስዘጋጅ ወደታች ስወርድ ግን በሙሉ እውቀት የተጻፈ የታምራትን ጽሁፍ አነበብኩ:: ታምራት የጻፈው በኔ እይታ በጣም ግልጽና እንደ ማብራሪያም በቂ ነው:: ቡሩክ አንተ የጻፍከው ትክክል ነው:: በተለይም በቅዱስ ሲኖዶስ ታይቶ ተገምግሞ ያልተወገዘን ሰው ተሀድሶ ነው ብሎ መፈረጅ ትልልቅ ስህተት ነው:: በጋሻውን ተሀድሶ ነው ያለ ሰው ግን ያለ  አይመስለኝም:: ካለም ትልቅ ስህተት ነው:: ነገር ግን ታምራት እንደጠቀሰው ቤተክርስቲያን በተሀድሶ እምነት አራማጆች እየተፈተነችበት ባለው በዚህ ወቅት በጋሻው ስብከቱ ላይ ትልቅ ጥንቃቄ ማረግ አለበት ቅዱስ ሲኖዶስ መድረክ ላይ መውጣት የለብህም ካለው ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝ ማክበር አለበት:: እውነት ለቤተክርስቲያን ቀናዒ ከሆነ አትስበክ ከተባለ ባይሰብክስ! ነገረ መለኮትን በተመለከት ታምራት በሚገባ ያለምንም ስህተት ስላብራራው ምንም መጨመር አልፈልግም:: ታምራት ሁለተኛው ማብራሪያህ ውስጥ ..."ቅዱስ ጴጥሮስ  “እግዚአብሄር በደሙ የዋጃትን ቤተ-ክርስቲያን “  ...የሚል አለ:: የቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት ውስጥ ይሄ ቃል ካለ አላውቅም (እርግጠኛ አይደለሁም):: "...እግዚአብሄር በደሙ የዋጃትን ቤተ-ክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት..." የሚል ግን የሐዋርያት ስራ ም.20 ቁጥር 28 ላይ አለ:: የሐዋርያት ስራን የጻፈው ደግሞ ቅዱስ ሉቃስ ነው:: ትምህርተ መለኮት ላይ የሰጠከን ማብራሪያ ሙሉ ነው ማስተዋል ለሚችል እጅግ በጣም ግልጽ ነው:: ስለ ምስጢረ ስላሴ ግልጽ ማብራሪያ የሚፈልግ እንዲያነብ እመክረዋለሁ:: ላንተም ቃለ ሕይውት ያሰማህ::
Quote   
06/20/2011 2:06 am

NEWBIE


Regist.: 06/16/2011
Topics: 0
Posts: 1
OFFLINE
ወንድም ብሩክ፣ ለማስተላለፍ የፈለከውን መልዕክት ተረድቸዋለሁ ሆኖም ግን አንዲት ቁምነገር እንድትገነዘብ እፈልጋለሁ፤ የተዋህዶ እምነታችን ራስ ክርስቶስ ነው ስለሆነም ምንም ፈተናው ቢበዛ ማንም ይህችን ሃይማኖት አያናጋትም ፡፡ በጋሻው አንድ ግለሰብ ነው እንዳልከው ምንአልባትም በአንድ ወቅትም ምን በርካታ ሰዎችን ወደ ቤተክርስቲያን መልሶ ሊሆን ይችላል ሆኖም ግን “ሰው” እንደሆነ አትዘንጋ፡፡ ይህ ዘምን የሃይማኖቱ እና የቤተክርስቲያን ነገር የሚያንገበግበው እና የሚቆረቁረው አብዛኛው ምዕመን ማንም ሳይነግረው የዘመኑ ሰባኪያን ነን ከሚሉት አንደበት በሚወጣው ቃል እንክርዳዱን ከስንዴው ለይቶ ያወቀበት ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ ትውልድ ቤተክርስቲያኑን እና እምነቱን ነቅቶ መጠበቅ እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ስለዚህ ስለ አንድ ግለሰብ ይህን ያህል አትኩሮት ሰጥተን ልንነጋገር አይገባም፣ በተጨማሪም እምነታችንንም በሰዎች ማንነት ላይ መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ ልናስተውል ይገባናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ወንድማችን ታምራት ይህንን ፎረም በመፍጠር እና እንዲሁም የቅድስት እምነታችንን ዶግማ እና ቀኖና በመከተል ስለምታካፍለን መንፈሳዊ ቁምነገሮች እና አስተምሮዎች ከልብ እናመሰግንሃለን፡፡ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ! የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት እና የጻድቃን ሰማዕታት ተራድኦ አይለይህ!
Quote   
06/20/2011 8:07 am

NEWBIE


Regist.: 06/20/2011
Topics: 0
Posts: 1
OFFLINE
የሚመልስልኝ ካለ

1. ለምን በጋሻው  ተሀድሶ ተበለው ከሚጠረጠሩ ሰዎች ጋር ሁሌ ህብረት ኖሮት  እናገኘዋለን? ለምሳሌ ከነ አሰግድ አባ ሰረቀ ጌታቸው ዶኒ ወዘተ

2. ለምን በጋሻው እስክ ለሊቱ 5 ሰዓት ድረስ ያስተምራል? የሚገርመው ሁለት የተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ላይ ከሌላ አገር ነው የሚመጣው ተብሎን  3 ሰዓት አካባቢ ነው የመጣው?(ቦሌ ገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፈረንሳይ ድልድይ ቅድስት ኪዳነምህረት )

3 ለምን በጋሻው (ትዝታው ሳሙኤልና ሌሎች) አለባበሳቸው የቤተ ክርስቲያን ልጅ አይመስሉም(ብታዩዋቸው ይቅርታ ፊልም ላይ የምናያቸውን ጋንግስተር ይመስላሉ)?

4. እነ በጋሻው satellite TV(ታኦሎጎስን) ከየት አምጥተው ከፈቱ (ገንዘቡ ውድ እንደሆነ ለESAT አዋጡ ሲጠየቅ አይተናል)?


Quote   
06/20/2011 3:54 pm

Administrator
NEWBIE


Regist.: 06/14/2011
Topics: 1
Posts: 4
OFFLINE
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እናድሳለን ከሚሉት ወገኖች አስተያየት፦

1) “እንደ እውነቱ ከሆነ በወንጌል እውነት ከታደሱ በኋላ በየጊዜው እየተመዘዙ የወጡት ምእመናኖቿና አገልጋዮቿ በውስጧ ቆይተው የተሐድሶን ሥራ እንዲሠሩ ቢደረግ ኖሮ፣ በወንጌል ተሐድሶ ያገኙ ክርስቲያኖች ለዓመታት የጸለዩበትንና የጓጉለትን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ በቅርብ ጊዜ ሊያዩ ይችሉ እንደ ነበር የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም፡፡” (ኆኅተ ብርሃን፣ መጋቢት 2002፣ ገጽ 15)
2) “ተሐድሶ እንቅስቃሴ በመሆኑ፣ እንቅስቃሴም ውጤታማና ትርፋማ ይሆን ዘንድ ዓላማን፣ ሒደትንና ግብን የያዘ ድርጊት እየተከናወነበት ያለ ሊሆን ስለሚገባው፣ ያለፈውና እየሆነ ያለው ግብረ ተሐድሶ ተመዝግቦ ለአሁኑና ለሚመጣው ትውልድ በሥነ ጽሑፍ ዳብሮና አምሮ ሊቀርብለት ይገባዋል፡፡” (ኆኅተ ብርሃን፣ መጋቢት2002፣ ገጽ 17)
3) “በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብተን አረሞችን በገሀድ ካልነቀልን ተሐድሶን እንዴት ልናመጣ እንችላለን? መባሉ አይቀርም፡፡ ዳሩ ግን ስሕተቶችን ፊትለፊት ሳይቃወሙ ስሕተቶች እንዲታረሙ ማድረግ የሚቻልባቸው የተፈተኑ መንገዶች አሉ፡፡ ለምሳሌም …” (ኆኅተ ብርሃን፣መጋቢት 2002፣ ገጽ 19)
4) “ከ2000 ዘመናት በላይ ያስቆጠረች የእኛ ቤተ ክርስቲያንማ እንዴት አብልጦ ተሐድሶ (መታደስ) አያስፈልጋት?” (መጥቅእ፣ ኅዳር 2002፣ ገጽ 15)
5) “ቤተ ክርስቲያናችን በክፉ ሰዎች ሴራ ዓላማዋን ስታለች፣ የሐዋርያትንም ትምህርት ገፍታለች፣ ስለ ሆነም ይህን የሐዋርያት ትምህርት በክፉዎች ምክንያት በመጣሱ በድፍረት ተሳስተሻልና ታረሚ ልንላት፣ በድፍረትም በሥልጣንም ሕዝቡን ልናስተምር ይገባል፡፡” (መጥቅእ፣ ኅዳር 2002፣ ገጽ 20)
6) “ቤተ ክርስቲያናችን በየሀገሩ የተነሣውን የተሐድሶ የወንጌል እሳት በተለይ በሐረር፣ በባሕር ዳር፣ በአዲስ አበባ፣ በማርቆስ፣ በጎንደር፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወሎ፣ በትግራይ፣ በባሌ ለማዳፈን ያን ሁሉ እልፍ አእላፍ ሠራዊት የቤተ ክርስቲያን አለኝታ ወጣት ወንጌል ባልገባቸው ምእመናንና ካህናት እያስደበደበች ለሌላ ድርጅት አሳልፋ ከመስጠት ይልቅ ስሕተቷን አርማ ልጆቿን በጉያዋ ብትይዝ ኖሮ ዛሬም ጭምር ጋብ ላላለው ፍጥጫ አትዳረግም ነበር፡፡” (መጥቅእ፣ ኅዳር 2002፣ ገጽ 16)
7) “ሕዝባችን በልማድና በባህል ሃይማኖትን መያዙና ይህን የያዘውን ሃይማኖት ለመጣልና ለማጣራትም በቂ እውቀት ስለሚጎድለው በራሱ አንብቦ መረዳት ስለማይችል …” (የሚያሳውቁት ሃይማኖትን ለማስጣል ነው ማለት ነው) (ይነጋል፣ 1997፣ ገጽ 144)
8) “የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት እግዚአብሔር ፍጹም ጨካኝ ስለሆነ ስለማይሰማንና በርኅራሄ ከእርሱ የተሻሉ ቅዱሳን በፊቱ ቆመው እንዲለምኑልን የእነርሱ ልመና ግድ ብሎት ስለሚምረን በአማላጅነት እንመን ይላል፡፡” (ይነጋል፣ 1997 ዓ.ም. ገጽ 123)
9) “ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ይህ የሰይጣን ማኅበር አሁን ወደ ነፍሰ ገዳይነት ሊገባ ራሱን እያዘጋጀ ነው፡፡” (ይነጋል፣ 1997 ዓ.ም.ገጽ 127)
10)ዊሊያም ብላክ የተባለው አሜሪካዊ ፓስተር አናሲሞስ በተባለው የጦማር መድረኩ ላይ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ማፈራረስ እንደሚቻልና በአሁኑ ወቅትም የእርሱና መሰል ድርጅቶች ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እየተዋጓት እንደሆነ “Struggle for the soul of the Ethiopian orthodox Church” በተሰኘው ጽሑፉ ላይ በሰፊው ገልጧል፡፡ የፕሮቴስታንት ጉዳይ አስፈጻሚ የሆነው የተሐድሶ አንቅስቃሴ ምን ማለት መሆኑን ለዓላማቸው መሳካት እንቅፋት ሆኖብናል ያለውን ነገር ሲናገር ገልጾታል፤ እንዲህ ሲል፡- “Working against both the ongoing creep of Western values and the attempts by Reformists to restore the church, a reactionary movement called Mahebere Kidusan and led by members of the hierarchy and priests and others, are seeking to fend off any changes and to preserve aspects of the Church which they feel are crucial to their identity and Ethiopia’s place in the world. … በሀገሪቱ ውስጥ እየተንሰራፋና ሥር እየሰደደ ያለውን ምእራባዊ ባህልና በተሐድሶ አራማጆች ቤተ ክርስቲያኒቷን ለማደስ የሚደረገውን ጥረት ሁለቱንም የሚቃወምና ለዚህም እየሠራ ያለ አድኃሪ የሆነ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል እንቅስቃሴ አለ፡፡ ይህ ማኅበርም ቤተ ክርስቲያንን ለመለወጥ የሚደረገውን ማንኛውንም ነገር ለመከላከልና ለራሳቸው ማንነትና ኢትዮጵያ በዓለም ስላላት ቦታ አስፈላጊ ነው የሚሉትን የቤተ ክርስቲያኒቷን ገጽታ ለመጠበቅ ይፈልጋሉ፡፡” http://www.Compassdirect.org/english/country.ethiopia/11092/

11) “ማቅ (ማኅበረ ቅዱሳን) ወደደም ጠላም ቤተ ክርስቲያኒቱ በእውነት በሚወዷትና የወንጌልን እውነት በሚያገለግሉ መምህራንና ሊቃውንት ይህንም እውነት ተቀብለው አምላካቸውን በንጹሕ ልብ ሆነው በሚያመልኩ፣ በተለይም መጪው ዘመን በትካሻቸው ላይ የወደቀባቸው ከመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን እየተመረቁ የሚወጡ የወንጌል አርበኞችና ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቁ ዘንድ እግዚአብሔር ጳጳሳት አድርጎ የሾማቸው አባቶች በሚወስዱት የማያዳግም እርምጃ ቤተ ክርስቲያናችን ተሐድሶን ታደርጋለች፡፡” (መጥቅእ፣ ኅዳር 2000፣ ገጽ 2)
www.eotc-mkidusan.org
................
ተሃድሶ በኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ

በዚህ ፎረም ከዚህ የሚከተሉት ጉዳዮች ይዳሰሱበታል
1) ተሃድሶ አለ?
2) ቤተ-ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል?
3) የተሃድሶ አላማ ምንድን ነው?
4
Quote   
Page 1 / 1
Login with Facebook to post
Preview